አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ስታርት አፕ ኢትዮጵያ” ለወጣቶች ሥራ ፈጠራ የተመቸ ከባቢን በመፍጠር ችግር ፈቺ የስራ መስኮችን ለመክፈት ያለመ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷“ስታርት አፕ ኢትዮጵያ” ለወጣቶች ሥራ ፈጠራ የተመቸ ከባቢን በመፍጠር ችግር ፈቺ የስራ መስኮችን ለመክፈት ያለመ ነው ብለዋል፡፡
“ወጣቶችን በፈጠራ ሃሳብ የተሞሉ የሀገራችን አንቀሳቃሽ ሞተሮች መሆናቸውን በመቀበል ሀሳባቸውን ወደ ተግባር የሚለውጡበት የዘርፉ ፖሊሲ ድጋፍም እጅግ አስፈላጊ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ካሉት ወቅታዊ ተግዳሮቶች ባሻገር ያለፉት ስድስት አመታት ስራችን የተለያዩ ማነቆዎችን በመፍታት ሰፋፊ ዕድሎች ለማስገኘት መንገድ የተከፈተበት ነበርም ነው ያሉት፡፡