የሀገር ውስጥ ዜና

በለውጡ የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በሃላባ ቁሊቶ እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

April 06, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በለውጡ የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በሃላባ ቁሊቶ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በድጋፍ ሰልፉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን የሃላባ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ በባለፉት ስድስት ዓመታት በለውጡ መንግስት የተመዘገቡ ድሎችን በቀጣይ በዘላቂነት ለማስቀጠል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።