የሀገር ውስጥ ዜና

ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ በሐረሪ ክልል ተካሄደ

By Melaku Gedif

April 06, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በለውጡ የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በሐረሪ ክልል ተካሄደ ፡፡

በድጋፍ ሰልፉ ከክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የተወጣጡ ነዋሪዎች፣ አርሶ አደሮች እና የመንግስት ሰራተኞች እየተሳተፉ ተሳትፈዋል።

ሰልፈኞቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት ባለፉት ስድስት የለውጥ ዓመታት በሰላም ፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር የተገኙ ስኬቶችን የሚገልጹ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ሰልፈኞቹ ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን፣ ለውጡን እናፀናለን፣ ድላችንን እንጠብቃለን ፣ለቀጣይ ስኬት በጋራ እንሰራለን እና ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም የሚሉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡