አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘመና አጋጥመዉ የነበሩ ስብራቶችን በአግባቡ የለየ፣ ስብራቶችን ለመጠገን መፍትሔ ያስቀመጠና በህዝብ ትግል የተወለደ ለዉጥ መጥቷል ሲሉ የዋግ ኽምራ ብሄረሰቡ ም/ አስተዳዳሪና የኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሹመት ጥላሁን ተናገሩ፡፡
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
በሰልፉ አቶ ሹመት ጥላሁን እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ ለዘመናን አጋጥመዉን የነበሩ ስብራቶችን በአግባቡ የለየ፣ ስብራቶችን ለመጠገን መፍትሔ ያስቀመጠ፣ የህዝቦችን ቀና ልብ መሠረት ያደረገና በርካታ ድሎችንም ያስመዘገበ በህዝብ ትግል የተወለደ ለዉጥ መጥቷል።
“በሀገራዊ ለዉጡ እንደ ሀገር ቀና ብለን እንድንሄድ የሚያስችሉ ያደሩ ፕሮጀክቶች ከነበሩበት ዉስብስብ ችግር በመላቀቅ ለፍጻሜ ደርሰዋል “ብለዋል።
“የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ዳር በማድረስ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ የኢኮኖሚ መሠረት እና ዘላቂ ጥቅም ያላቸዉን ፕሮጀክቶች በማቀድ እና በመፈጸም ያሳየነዉ ዉጤት የታለመዉ የብልጽግና ጉዞ አይቀሬ መሆኑን የሚያሳይ ነባራዊ ሀቅ ነዉም” ብለዋል፡፡
መላዉ የብሔረሰብ አስተዳደሩ ህዝብ የክልሉን ሰላም ወደ ተሟላ ደረጃ ለማድረስ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥሉ መጠየቃቸውን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡