የሀገር ውስጥ ዜና

የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ ተገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

April 09, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ የሚከበረውን የዒድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ከጠዋቱ 12 ሠዓት ላይ ዘጠኝ ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሕብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው ሲልም የሚኒስቴሩ የሥነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡