አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ፆም ወቅት ያከናወነውን መልካም ተግባር ከፆም ውጪ ባሉ ጊዜያትም ሊያጠናክር እንደሚገባ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ተናገሩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ለእስልምና እምነት ተከታዮች የ1 ሺህ 445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
በመልእክታቸውም÷ታላቁ የረመዳን ፆም ወር ህዝበ ሙስሊሙ ከፈጣሪው ጋር የጠበቀ ግኑኝነት የሚያደርግበትና መልካም ተግባራትን የሚያከናውንበት የተቀደሰ ወር ነው ብለዋል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ፆም ወቅት ሲያከናውን የቆየውን መልካም ተግባር ከፆም ውጪ ባሉ ጊዜያት አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ማሳሰባቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የመደጋገፍ፣ የመረዳዳትና የመቻቻል እሴትን በማጠናከር እና መልካም ተግባራትን በመፈፀም ሊሆን ይገባልም ብለዋል፡፡