አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቡሩንዲ ፕሬዚደንት ፒየር ንኩሩንዚዛ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት፥ “ፕሬዚደንት ፒየር ኡንኩሩንዚዛ በድንገት ሕይወታቸው በማለፉ የተሰማኝን ሀዘን እገልጻለሁ” ብለዋል።
ለቤተሰባቸው እና ለብሩንዲ ሕዝብ መጽናናትንም ተመኝተዋል።
የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፕዬሬ ንኩሩንዚዛ በ55 ዓመታቸው በድንገተኛ የልብ ህመም በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል።
በአውሮፓውያኑ በ1963 የተወለዱት ፕሬዚዳንት ፕዬሬ ንኩሩንዚዛ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2005 ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ቡሪንዲን መርተዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።