አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ስለ ምጣኔ ሀብት ማገገምና ስለ አዲስ የዕድገት አቅጣጫ ባዘጋጀው “ታላቁ ዳግም ማስጀመሪያ” የኦንላይን ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡
በዚህ ወቅትም የወረርሽኙን ዓለም አቀፋዊ ውስብስብንነት እና ለመላመድ ያለውን ፈተና ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ችግሩ ሊፈታ የሚችለው በጋራ ርምጃዎች እና በዓለም አቀፍ ትብብር ብቻ ነው ብለዋል፡፡