የሀገር ውስጥ ዜና

በተሻሻለው የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ዙሪያ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

April 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተሻሻለው የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ዙሪያ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

መድረኩ የተሻሻለው የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ የሚያመጣቸው ሀገራዊ ፋይዳዎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አቶ መላኩ አለበል÷ ፖሊሲው በግሉ ዘርፍ የሚመራ፣ የመንግስትን ሚና በግልፅ የለየ እና ለወጪ ተኪ ምርት የተመጣጠነ ትኩረት የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጠናከረ የግብዓት ምርት ልማት የሚደገፍ፣ ለምርት ጥራት ስራ አመራር ትኩረት የሰጠ ፖሊሲ እንደሆነም አስገንዝበዋል።

ለቴክኖሎጂ ልማት፣ በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር እና ብቁ የሰው ሃይል ለአምራች ዘርፍ መፍጠር የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ እና ኤፍሬም ምትኩ