አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው የሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሦስተኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ-ጉባዔውን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የኮሪደር ልማት የአንድ ወር ከ15 ቀን አፈፃፀም ሪፖርትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም የአሥተዳደሩ ተጨማሪ የበጀት አዋጅ ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል መባሉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ጉባዔው የምክር ቤቱ የተሻሻለ የአባላት ሥነ-ምግባር እና ደንብ ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ተጠቁሟል፡፡