አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ዛሬ በ”ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” የዲጂታል ቴሌቶን ተሳትፎ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷” ዛሬ የ”ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” የዲጂታል ቴሌቶን ተሳትፎ ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ” ብለዋል፡፡
ለጋራ ጥቅም በጋራ ስንቆም ድንቅ እንሆናለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷በጋራ ትርጉም ያለው በጎ ተፅዕኖ መፍጠር እንችላለን ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
እስካሁን በ#ጽዱኢትዮጵያ ቴሌቶን ያልተሳተፉም ዛሬ በቀሪዎቹ ሰዓታት፣ በመጪዎቹ ቀናት እና ሳምንታት እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡