የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ ለሁለት የእምነት ተቋማት ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረቡ አዋጆችን አፀደቀ

By Tibebu Kebede

June 11, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትንና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረቡ ረቂቅ አዋጆች አፀደቀ።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት16ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።