ዓለምአቀፋዊ ዜና

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት የተጣለን ዕገዳ በመጣሳቸው ተቀጡ

By Meseret Awoke

June 11, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ መንግስታቸው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ባለማክበራቸው ተቀጡ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለቅጣት የተዳረጉት ከሳምንት በፊት በአገሪቱ ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ በምትገኘው ኼሜለኒስካይ ከተማ ወደሚገኝ ካፍቴሪያ መሄዳቸውን ተከትሎ ነው።

በከተማዋ የሚገኙ ምግብና መጠጥ ቤቶች ገዝቶ ከመሄድ ውጪ በቦታው ሆኖ መስተናገድ የተከለከለ ሲሆን እገዳውን ተላልፈው የተገኙት የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት በካፊቴሪያው ቁጭ ብለው ሲስተናገዱ ታይተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ በጽህፈት ቤታቸው ካፍቴሪያው የፊት ጭምብል ሳያደርጉ የሚያሳይ ፎቶ ይፋ መድረጉን ተከትሎ ተቀጥተዋል።

ሆኖም ፕሬዝዳንቱ የተጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት “ትክክለኛ እርምጃ ነው የተወሰደብኝ” ያሉ ሲሆን ሆኖም የገንዘብ መጠኑን ከመናገር ተቆጥበዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ