የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ማዕድ አጋሩ

By Amele Demsew

April 30, 2024

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጪውን የትንሣዔ በዓል ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ማዕድ አጋሩ፡፡

የማዕድ ማጋራቱ ዝቅትኛ ገቢ ካላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በተጨማሪ ጽሕፈት ቤቱ የሚያሳድጋቸው አሳዳጊ የሌላቸው ሕጻናትንም ያካተተ ነው፡፡