የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ‘ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄን ተቀላቀለ

By Tamrat Bishaw

May 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ‘ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄን ተቀላቀለ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ተደርጎ “ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለውን የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን በመደገፍ 50 ሺህ ብር ገቢ አድርጓል።

ንቅናቄው ለከተማ ውበት እና ለኅብረተሰቡን ጤና መጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ያለው የፌዴራል ፖሊስ፤ መላው ህዝብ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል።