አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 46 በርሚል ነዳጅ መያዙን የሚዛን አማን ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር አዳነ አለማየሁ እንደገለጹት÷ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ከተያዘው ነዳጅ ውስጥ 35 በርሚሉ ናፍታ ሲሆን 11 በርሚሉ ደግሞ ቤንዝል ነው፡፡
በተሽከርካሪ ተጭኖ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ በተያዘው ነዳጅ ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የሕገ-ወጥ ነዳጅ ግብይት መበራከት የግብይት ሥርዓቱን ከማወክ ባለፈ በህብረተሰቡ ዘንድ የቅሬታ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን አንስተዋል፡፡
በቀጣይ ማደያዎች በመንግስት ድጎማ የሚመጣው ነዳጅ ላይ የሚያደርጉትን ሕገ-ወጥ ግብይት በማቆም በተቀመጠው አሰራር መሰረት ጤናማ የግብይት ሒደት እዲከተሉ አስገንዝበዋል፡፡
ደንቡን በሚጥሱት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውንም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡