የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 180 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

May 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ሥራ 1 ሺህ 180 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾች ውስጥ 1 ሺህ 98 ወንዶች፣ 79 ሴቶች፣ 3 ጨቅላ ህፃናት  እንዲሁም 228  እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተጠቅሷል።

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡