የሀገር ውስጥ ዜና

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ ባሕርዳር ገባ

By Melaku Gedif

May 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ ባሕርዳር ከተማ ገብቷል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የጣና ሐይቅ ፈርጧ፣ የበርካታ ደሴቶች መናኸሪያ፣ የጢስ አባይ ፏፏቴ መገኛ እና የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ በሆነችው ውቢቷ ባሕርዳር ገብተናል ብለዋል።

ልዑኩ ባሕር ዳር ሲደርስም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና ካቢኔያቸው አቀባበል አድርገውለታል።