የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

By Melaku Gedif

May 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከ1 ቢሊየን 428 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ኢክራም አብዱልቃድር ÷ ገቢው ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ የታክስና ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

ገቢው ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ248 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

ቢሮው የገቢ አሰባሰቡን የበለጠ ለማጎልበትና ሕገ-ወጥ ንግድን ለመዋጋት በዲጅታል የተደገፈ አሰራርን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡