የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ ከድር ጁሃር የትንሳኤ በዓልን በመደጋገፍ ማክበር እንደሚገባ ገለጹ

By ዮሐንስ ደርበው

May 04, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትንሳኤ በዓልን ስናከብር የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችንን በማጠናከር ሊሆን ይገባል ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ።

ከንቲባው ለትንሳኤ በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልዕክት÷ ለክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

በዓሉን ስናከብርም ለችግር የተዳረጉ ሕጻናትና አረጋውያንን በመርዳት ሊሆን ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሰላም፣ የአንድነትና የልማት ተግባራት በተቀናጀ መንገድ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።