አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕመኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን በማገዝ ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል ዋና ጸሐፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩ አስገነዘቡ፡፡
ዋና ጸሐፊው ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም÷ ምዕመኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር ዕርዳታና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች በማገዝ ሊሆን ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በክርስቶስ ትንሳኤ ሁሉም በፍቅር ልብና በይቅርታ ለሰላምና አብሮነት በመጸለይ በዓሉን እንዲያከበርም ጠይቀዋል፡፡