ስፓርት

አርሰናል የዋንጫ ተፋላሚነቱን አጠናከረ

By Tamrat Bishaw

May 04, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሰናል በርንማውዝን 3 ለ 0 በማሸነፍ የዋንጫ ተፋላሚነቱን አጠናክሯል፡፡

በ36ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል በርንማውዝን በረታበት ጨዋታ ቡካዮ ሳካ፣ ትሮሳርድ እና ራይስ ጎሎቹን ማስቆጠር ችለዋል፡፡

መድፈኞቹ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎም ነጥባቸውን 83 በማድረስ ፕሪሚየር ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ፡፡