የሀገር ውስጥ ዜና

በየአካባቢያችን አቅም ያጠራቸውን ወገኖቻችን ልናስባቸው ይገባል -አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

By Feven Bishaw

May 05, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ልብስ ለብሰው ግን ደግሞ ሆዳቸው ባዶ የሆኑ አቅም ያጠራቸውን ወገኖቻችን በየአካባቢያችን ልናስባቸው ይገባል ሲሉ ተናገሩ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ቁጥር 4 በመገኘትለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ መሰል ተግባር በምናምነው ሃይማኖት፣ በመንፈሳዊ እና በዓለማዊውም የሚደገፍ ተግባር መሆኑን ጠቅሰው አቅም ካጠራቸው ጋር ያለንን ማካፈል ከተረፈው ብቻ ሳይሆን ካለው የሚደረግ ተግባር እንደሆነም አንስተዋል።

ይህንን የመሰለውን ለአቅመ ደካሞች ማዕድ የማጋርት በጎ ተግባር እየደገፉ ያሉ ተቋማት እና አካላት ሊመሰገኑ እንደሚገባ ደግሞ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

በይስማው አደራው