አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ አፈፃፀም ላይ በዛሬው ዕለት መምከሩን አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ አፈፃፀም ጋር የተያያዙ ሰፋ ያለ መጠነ-ርዕይ ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል ብለዋል፡፡