የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

May 07, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ከጠዋቱ 2 ሠዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

አደጋው የደረሰው ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ የዕርዳታ እህል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሸከርካሪ መንገድ ስቶ በመገልበጡ ነው ተብሏል፡፡

የተሽከርካሪውን መገልበጥ ተከትሎም መንገድ ላይ በንግድ ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ ሶስት ሴቶች እና አሽከርካሪው ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡

የአደጋው መንስኤም በፍጥነት ማሽከርከር መሆኑ ነው የተመላከተው፡፡

በነጌሶ ከድር