የሀገር ውስጥ ዜና

የታላቁ ነጃሽ 00 መንደር ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐግብር እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

May 07, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ ነጃሽ 00 መንደር ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤ እና የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፥ ከአል ነጃሺ መልሶ ግንባታ እና ልማት ኢኒሼቲቭ ጋር በመሆን ነው መርሐ ግብሩ እየተካሄደ የሚገኘው።

በመርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ አደም አብዱርቃድር፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ ዘሃራ ዑመርን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖቱ መምህራን፣ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

በመራዖል ከድር