የሀገር ውስጥ ዜና

በነቀምቴ ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

May 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በነቀምቴ ከተማ ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

በድጋፍ ሰልፉም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ስኬቶችን የሚገልጹ መልዕክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ፡፡

በዚህም ለውጡን ለማጽናት ማንኛውንም መስዋዕትነት እንከፍላለን!፣ ወለጋ የሰላምና የብልጽግና ምድር!፣ ለውጡን ለማጽናት ማንኛውንም መስዋዕትነት እንከፍላለን!፣ ድላችንን እንጠብቃለን ለቀጣይ ስኬት በጋራ እንሰራለን! እና መሪያችን ብልጽግናን በማሳካት ህልምህን እውን እናደርጋለን! የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

በተጨማሪም ሰላማችንን በመጠበቅ ድላችንን እናጸናለን!፣ በሰላምና በይቅርታ መንገድ ሁሉም አሸናፊ ነው!፣ በሰላምም በልማትም ተምሳሌት ሆነን እናኮራሀለን!፣ ከብልጽግና ጉዟችን የሚገታን ፈተና አይኖርም! እና የአሸባሪው ሸኔ ድብቅ ዓላማ የኦሮሞ ሕዝብን ወደ ባርነት መመለስ ነው! የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል።