የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የትራንስፎርሜሽናል ዕቅድ ዝግጅት መድረክ መካሄድ ጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

May 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት የትራንስፎርሜሽናል ዕቅድ ዝግጅት መድረክ መካሄድ ጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በመድረኩ አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተመራጭ ከተማ ለማድረግ በሚያስችሉ በተመረጡ ስድስት አጀንዳዎች ላይ ስልጠና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

በዚህም የትራንስፎርሜሽን እቅድ ዝግጅት የሚከናወን ሲሆን በስልጠናው ዓለም አቀፍ የዘርፉ ባለሙያዎች ለአመራሩ ስልጠና እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

ሀገራችንን ለማበልጸግ በሁሉም ዘርፍ ያለ እረፍት መስራታችን ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉም በመልዕክታቸው አመልክተዋል።