የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ክልል ሕዝብ በ #ጽዱኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶ ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበ

By ዮሐንስ ደርበው

May 12, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ የክልሉ ሕዝብ በ #ጽዱኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ለጽዱ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ ያለመ የዲጂታል ቴሌቶን እየተካሄደ ነው፡፡

ይህን አስመልክተው አቶ ኦርዲን ባስተላለፉት መልዕክት÷ የንቅናቄው ንጹህ አካባቢን በመፍጠር ለትውልድ ለማስተላለፍ ያለመ በመሆኑ የክልሉ ሕዝብ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለዓላማው መሳካት አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል፡፡