አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የሐረር ቀንን በስኬት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጀት መደረጉን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷በዛሬው ዕለት 26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀንን አስመልክቶ የሚከናወኑ ተግባራትን ገምግመናል ብለዋል፡፡
በዚህም በዓሉ አብሮነትን በሚያጠናክርና ልማትን በሚያፋጥን እንዲሁም የዳያስፖራውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በሚያጠናከር መልኩ እንዲከበር የጋራ መግባባትላይ መደረሱን አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ሲምፖዚዬሞች፣ የባህል ትርዒቶች፣ ኤግዚብሽንና ባዛሮች፣ የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ የአረንጓዴ አሻራ እና የበጎ አድራጐት ሥራዎችን ጨምሮ ሌሎች ኩነቶች እንዲከናወኑ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን ስኬታማ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡም ርዕሰ መስተዳደሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡