የሀገር ውስጥ ዜና

ከተለያዩ ሀገራት ልምድ ለመቅሰም የመጡ የሥራ ኃላፊዎች የሕጻናት መዋያዎችን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

May 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ልምድ ለመቅሰም ወደ አዲስ አበባ የመጡ የሥራ ኃላፊዎች በመዲናዋ የሚገኙ የሕጻናት መዋያዎችን እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ጎበኙ፡፡

በመዲናዋ 597 የሕጻናት መዋያዎች በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ፣ በግል እና በመንግሥት ተቋማት ውስጥ መገንባታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በማቆያዎች ለሚገኙ ሕጻናትም÷ የተመጣጠነ ምግብ፣ የሞግዚት አገልግሎት፣ የጤና ክትትል፣ ትምህርት በጨዋታ መስጠት፣ የእናቶች ምክር አገልግሎት እና የተሟላ እድገት እንዲኖራቸው ልዩ ክትትል እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል፡፡

አዲስ አበባ ሕጻናትን ለማሳደግ ምርጧ አፍሪካዊት ከተማ የማድረግ ሥራችን ዕውቅና አግኝቶ ለሌሎች ልምድ የምናካፍልበት ደረጃ ላይ በመድረሳችንም ደስ ብሎናል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም የሕጻናት መዋያዎችን 1 ሺህ እንዲሁም የመጫወቻ ቦታዎችን 12 ሺህ ለማድረስ በርትተን እንሥራ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡