አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የማኔጅመንት አባላት ለ #ጽዱኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ንቅናቄውን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡
ንቅናቄው ሰዎች ንጽህናውን በጠበቀ ቦታ በመጸዳዳት አካባቢን ንጹህ የማድረግ ባህልን እንዲያሳድጉ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎች እንዲሠሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መሆኑ ይታወቃል።
ለ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ዜጎች ተሳትፎ ማድረጋቸውን የቀጠሉ ሲሆን÷ በትናንትናው ዕለት ብቻ በተካሄደ ዲጂታል ቴሌቶን በአንድ ጀምበር ከ154 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ይታወሳል፡፡