የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 179 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Mikias Ayele

May 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ ችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 179 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ÷ ከእነዚህ ውስጥም 14 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ  እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡