የሀገር ውስጥ ዜና

የክልሉ የብልጽግና ጉዞን ለማሳለጥ ተቋማት በዕቅዶች ላይ በቅንጅት እንዲሠሩ ተጠየቀ

By ዮሐንስ ደርበው

May 14, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልልን የብልጽግና ጉዞን ለማሳለጥ ተቋማት በዕቅዶች ላይ ቅንጅትና ትብብር መፍጠር እንዳለባቸው ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ኢብራሂም ዑስማን አሳሰቡ፡፡

የሶማሌ ክልል የመንግስት የልማት ድርጅቶች የበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡

ምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ በመድረኩ ላይ እንዳሉት÷ የታቀዱ ሥራዎች፣ የተሠሩ ሥራዎች፣ ታቅደው ያልተሳኩ ሥራዎች እና በሥራ ሂደት ውስጥ ያጋጠሙ እንቅፋቶችና መፍትሔዎች በጥልቀት ይገመገማሉ፡፡

በቀጣይ የክልሉ የብልጽግና ጉዞን ለማሳለጥ ተቋማት በዕቅዶች ላይ ቅንጅትና ትብብር መፍጠር እንዳለባቸው ማስገንዘባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡