የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአምባሳደር ማይክ ሀመር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

May 14, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷ በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አምባሳደር ምስጋኑ ÷በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና የመልሶ ማቋቋም ሂደት እንዲሁም የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር አለም አቀፍ ድጋፍ እንደሚያስፈልግም በውይይቱ ተጠቁሟል።