የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 141 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Meseret Awoke

May 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በተከናወኑ ሦስት በረራዎች በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 141 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከ24 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉም ተገልጿል፡፡