የሀገር ውስጥ ዜና

ም/ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ከከምባታ ዞን ወጣቶች ጋር እየመከሩ ነው

By Feven Bishaw

May 18, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ከከምባታ ዞን ወጣቶች ጋር በሰላምና በልማት ጉዳዮች ላይ በዱራሜ ከተማ እየተወያዩ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ ከምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ ሌሎች የክልሉና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከዞኑ የተውጣጡ ወጣቶች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከከምባታ ዞን ወጣቶች ጋር በሰላም፣በልማት እና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ እንደሆነ ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡