ዓለምአቀፋዊ ዜና

በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ41 ሺህ አልፏል

By Tibebu Kebede

June 13, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

አሁን ላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከብሪታንያ በመብለጥ ከ41 ሺህ አልፏል።

አሃዙ ከአሜሪካ ቀጥሎ ዓለም ላይ ሁለተኛው ሆኗል።

አሁን ላይ በሃገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ 828 ሺህ 810 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው፥ ወደ 42 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።

ይሁን እንጅ በሃገሪቱ ካለው የመመርመር አቅም ውስንነት አንጻር ቫይረሱ በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት ከተነገረው ይልቅ ከፍተኛ መሆኑንም ነው ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች የሚያመላክቱት።

ከዚህ ባለፈም የቫይረሱ ስርጭት በቀጣዮቹ ሳምንታት “ከፍተኛ” የሚባል ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል ከመባሉ ጋር ተያይዞ ቀጣዮቹ ሳምንታት ለሃገሪቱ ፈታኝ ናቸው እየተባሉ ነው።

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ ከቫይረሱ ይልቅ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት በተጎዳው ኢኮኖሚ ላይ ትኩረት ማድረጋቸው እየተነገረ ነው።

ይህ መሆኑ ደግሞ ለቫይረሱ ስርጭት “ግድ የላቸውም” በሚል ወቀሳው እና ትችቱ በርትቶባቸዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ