የሀገር ውስጥ ዜና

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖን ጎበኙ

By Melaku Gedif

May 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሚኒስትሮች ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖን ጎብኝተዋል።

የስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ መከፈቱ ይታወቃል።

ዓመታዊው ኤክስፖው “ሳይንስ በር ይከፍታል፤ ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፤ ፈጠራ ወደፊት ያራምዳል” በሚል መሪ ኃሳብ በሳይንስ ሙዚየም እስከ ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ትኩረቱን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያደረገው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ በርካታ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ተቋማትን በማሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በኤክስፖው የመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሁም ስታርት አፖች የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን ለዕይታ አቅርበዋል።