የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ አበባና የቻይናዋ ቾንግኪንግ ከተማ የእህትማማች ስምምነት ተፈራረሙ

By Meseret Awoke

May 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ እና የቻይናዋ ቾንግኪንግ ከተማ የእህትማማች ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በቻይና ቾንግኪንግ ከተማ የሥራ ጉብኝት አካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅትም በአዲስ አበባ እና በቾንግቺንግ ከተማ መካከል የእህትማማች ስምምነት መፈረሙን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

የከተሞቹ አጋርነት በንግድ፣ በትምህርት እና በባህል ልውውጥ ያለውን ትብብር ማሳደግ እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡