የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 199 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Mikias Ayele

May 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 199 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾች ውስጥ 1 ሺህ 159 ወንዶች፣ 19 ሴቶች፣ 21 ጨቅላ ሕጻናት እና 12 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ ያሉ እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶችን ለልማት ማዋል የሚቻለው ተቀራርቦ በመስራት ሊሆን እንደሚገባ መግለፃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡