የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከቻይና ሲሲሲሲ ካምፓኒ ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

May 23, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይና ኮሙኒኬሽን እና ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (ሲሲሲሲ) ሊቀመንበር ዋንግ ቶንግዙን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመላው ኢትዮጵያ ባሉ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያለውን ሲሲሲሲ የበለጠ ትኩረት እና ኢንቨስት ሊያደርግባቸው የሚችሉ ሀገራዊ እምቅ ሃብቶችን አስመልክቶ ውይይት ማድረጋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡