የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ 9ኛው ከተማ አቀፍ የሣይንስ ፈጠራ ዐውደ-ርዕይ መካሄድ ጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

May 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ 9ኛውን ከተማ አቀፍ የሣይንስ ፈጠራ ዐውደ-ርዕይ ማካሄድ ጀመረ፡፡

በዛሬው ዕለት በወዳጅነት ዐደባባይ መካሄድ የጀመረው ዐውደ-ርዕዩ ለሦስት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

ዐውደ-ርዕዩ “በፈጠራ ሥራ የዳበረ ትውልድ ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና’’ በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ መሆኑን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

ከመንግሥትና ከግል ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ ተማሪዎችና መምህራን የተሠሩ የፈጠራ ሥራዎች በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲጎበኙ ለዕይታ መቅረባቸውም ተጠቅሷል፡፡