የሀገር ውስጥ ዜና

አየር መንገዱ ከሰኔ 10 ጀምሮ ወደ ነቀምቴ በረራ ይጀምራል

By Feven Bishaw

May 25, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ በረራ እንደሚጀምር ገለጸ።

የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያዴቻ እንደገለጹት÷ አየር መንገዱ እያደገ የመጣውን የሀገር ውስጥ የደንበኞች ፍላጎት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ነው።

በዚህም ከመጪው ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ነቀምቴ በረራ እንደሚጀምር ገልጸው በረራው በሣምንት አራት ጊዜ እንደሚካሄድ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አየር መንገዱዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን ከማስፋት ባሻገር የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎችን ለማስፋት እያደረገ ባለው ጥረት በ2035 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎቹን ወደ 32 ለማሳደግ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡