የሀገር ውስጥ ዜና

የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ዝግጅቶች በከፍተኛ ርብርብ በመከናወን ላይ ይገኛሉ – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By Melaku Gedif

May 26, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ዝግጅቶች በከፍተኛ ርብርብ በመከናወን ላይ ይገኛሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ የችግኞች ተከላ እየተቃረበ እንደመሆኑ ዝግጅቶች በከፍተኛ ርብርብ በመከናወን ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

የተከላ ስፍራዎች ተለይተው በመዘጋጀት ላይ ሲሆኑ ችግኞችም በተከታታይነት በመፍላት ላይ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።

ዓመታዊ መርሃ ግብራችን የአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት መርህን የሚያስፋፋ፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚከላከል፣ የደን ጭፍጨፋን ጉዳት የሚቀለብስ፣ የመሬት መራቆትን የሚቀንስ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የማኅበረሰብ አባላት፣ ትምህርት ቤቶች እና ተቋማት በጋራ በመቆም በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዛፎች እንዲተከሉ የተሰራበት ንቅናቄ ነው በማለት ገልጸዋል።