የሀገር ውስጥ ዜና

የ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ አካል የሆነ የጽዳት ሥራ በባሕር ዳር ከተማ ተካሄደ

By ዮሐንስ ደርበው

May 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ #ጽዱኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ አካል የሆነ የከተማ ጽዳት ሥራ “ደጀን አፀዳለሁ ከተማዬን አስውባለሁ” በሚል መሪ ሐሳብ በባሕር ዳር ከተማ ተካሄደ።

በጽዳት ሥራውም የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው፣  የአሥተዳደሩ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

ከንቲባው ባስተላለፉት መልዕክትም የአካባቢ ብክለትን በመከላከል ፅዱ ባሕር ዳርን በመገንባት የከተሞች ተምሳሌት ማድረግ ይገባል ማለታቸውን የአሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ባሕር ዳርን ውብ፣ ለኑሮና ለቱሪዝም ተስማሚ ለማድረግ÷ የፅዳት፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የአካባቢ ብክለት ጥበቃ፣ የፍሳሽ አወጋገድና መሰል ተግባራትን በትጋት ማከናወን ይጠበቅብናል ብለዋል።

#ጽዱኢትዮጵያ