የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን አስጀመሩ

By ዮሐንስ ደርበው

May 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ የ206/17 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ-ግብርን በጋምቤላ ከተማ አስጀመሩ።

ርዕሰ መሥተዳድሩ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የበጎ ፈቃድ ሥራ ንቅናቄ እርስበርስ የመደጋገፍ ባህልን የሚያዳብርና ለመጪው ትውልድም መልካም እሴትን የሚያሸጋግር ሥራ ነው ብለዋል።

በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ የአቅመ ደካማ ወገኖቻንን ቤት ከማደስ በተጨማሪ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር እናከናውናለን ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚከናወኑ ተግባራት ላይም ተቋማት፣ ባለሀብቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ በጋምቤላ ከተማ በአምስቱም ቀበሌዎች የተጀመረው የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ በዞንና በወረዳ ደረጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል፡፡