የሀገር ውስጥ ዜና

በአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ እየተሳተፈች ነው

By Meseret Awoke

May 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በኬንያ ናይሮቢ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

የዚህ ዓመታዊ ጉባኤዎች መሪ ሃሳብ “የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድንና የዓለም አቀፍ የፋይናንሺያል አርክቴክቸር ለውጥ” ነው።

በጉባኤው፥ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ከኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ጋር መገኘታቸውን ናይሮቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።