የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

By Melaku Gedif

June 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዳማ ከተማ ተካሄዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የአዳማ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

አቶ አብዱልሀኪም በዚሁ ወቅት÷በአደማ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት እድሳት አስጀምረዋል።

በተመሳሳይ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚከናወን የህፃናት መዋያ ማዕከል ግንባታም ተጀምሯል።

በክልሉ በተጀመረው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት12 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች እንደሚሳተፉ ተመላክቷል፡፡

በዚህም 46 ነጥብ 6 ቢለየን ብር የሚገመት ሥራ በማከናወን 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጿል፡፡

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳትና ግንባታ፣ የአካባቢ ጽዳት፣ ችግኝ ተከላ፣ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጭምሮ በተለያዩ ዘርፎች እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡

በሌሊሴ ተስፋዬና ኦሊያድ በዳኔ