የሀገር ውስጥ ዜና

የመጪው ጊዜ ግንኙነታችን የበለጠ ጠንካራና ዘርፈ ብዙ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነቴ የፀና ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By Mikias Ayele

June 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያ የመጪው ጊዜ ግንኙነት የበለጠ ጠንካራ እና ዘርፈ ብዙ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነቴ የፀና ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ይኦል ላደረጉልን አቀባበል አመሰግናለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያ ትስስር ከስድሳ አመታት በላይ ያስቆጠረ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ የመጪው ጊዜ ግንኙነታችንም የበለጠ ጠንካራ እና ዘርፈ ብዙ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነቴ የፀና ነው ሲሉ ገልጸዋል።